Resources
የሲያትልትምህርትቤቶችየቤተሰብመርጃዎች
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ለእያንዳንዱ ተማሪ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ቁርጠኛ ነው።
እኛ የሲያትል ከተማ እናገለግላለን።ተማሪዎቻችን ከ140 በላይ ቋንቋዎች ወይም ዘዬዎችን ይናገራሉ። በቤተሰቦች እና በተማሪዎች በብዛት የሚነገሩ ከፍተኛ አምስት ቋንቋዎች የሚከተሉት ናቸው: ስፓኒሽኛ፣ሶማሊኛ፣ቻይንኛ፣ቬትናምኛ እና አማርኛ።
ትምህርት ቤቶቻችን 62 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣10 K-8 ትምህርት ቤቶች፣11 መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 17 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያካትታሉ።
የብዝሃ ቋንቋ ገፅ
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች ተማሪዎቻቸውን እንዲያግዙ ለመርዳት ቁልፍ በሆኑ ድረ-ገጾች ላይ በኮምፒዩተር ሳይሆን በሰው የተተረጎሙ ጠቃሚ መረጃዎችን ያትማል።
ሁሉም ድረ-ገጾቻችን በዚህ መንገድ አይታተሙም።የቋንቋ አገናኞች የሌሉት ድረ-ገጽ ከጎበኙ፣በላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ የሚገኘውን የጉግል ትርጉም መጠቀም ይችላሉ።
ለሲያትል ትምህርት ቤቶች አዲስ
ወደ ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች እንኳን በደህና መጡ!
በተሸላሚ ትምህርት ቤቶቻችን፣በታላላቅ አስተማሪዎቻችን፣በጠንካራ የአካዳሚክ ፕሮግራሞቻችን እና የማህበረሰባችን ተሳትፎ እንኮራለን።
ልጅዎ ነሐሴ 31 ላይ 5 ዓመት ይሆነዋል(ይሆናታል)? ስለዚህ በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ወደ ኪንደርጋርተን ለመመዝገብ ጊዜው አሁን ነው።!
ልጄ ተመዝግቧል።ቀጥሎ ምንድን ነው?
መርጃዎች
ዜና
የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች
የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች…የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበጀት ማሻሻያ እና ቀጣይ እርምጃዎች
የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበጀት ማሻሻያ እና ቀጣይ እርምጃዎች ውድ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች፣ሰራተኞች እና ማህበረሰብ፣ ለተማሪዎቻችን እና ለት/ቤቶቻችን ያላሰለሰ ጥረት ስላደረጉልን እናመሰግናለን።እነዚህን ፈታኝ ጊዜዎች ለማለፍ ስንዳስስ ለምታደርጉልን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።…ስለ በደንብ የተደራጁ ትምህርት ቤቶች አስመልክቶ ወቅታዊ መረጃ
የትምህርት ስርዓታችንን ትክክለኛ መጠን ለማድረግ እርምጃዎችን እየወሰድኩ ለ2025-26 የትምህርት ዘመን የበጀት ጉድለትን ለመፍታት የሚረዳ የተሻሻለ እቅድ አዘጋጅቻለሁ።በዚህ ክለሳ መሰረት፣…አግኙን
የድር ገፅ ግብረ መልስ የድር ገጽ ግብረ መልስ ወይም አስተያየቶች ሊልኩልን ይችላሉ።
አጠቃላይ ጥያቄዎች ጥያቄዎች ወደ ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች በእንነጋገር ቅጽ በኩል መላክ ይችላሉ።